
March 23, 2010
March 10, 2010
በፍቅርሽ ታስሬ
የኋሊት ስጎተት በፍቅርሽ ታስሬ፤
ወደፊት መራመድ እያቃተው እግሬ።
አሁንም አሁንም ቆሜ አያለሁ ዙሬ፤ምንም ልቤ ቢፈራ ባይቀር መጠርጠሬ፤
እስከ ዛሬ ድረስ በህይወት መኖሬ፤ተስፋ ሆኖኝ ነበር ፍቅርሽና ፍቅሬ።
ግን እውነት ከሆነ የነገሩኝ ወሬ፤
መኖር አልፈልግም ሞቼ ልደር ዛሬ።
ዱብ እዳ ወድቆብኝ ለሸክሙ አስቸጋሪ፤ ጨንቆኝ ስለፈልፍ እንደ ቀባዣሪ፤
ባንች እምነት የሌለኝ፤ ብመስል ጠርጣሪ፤ መሆንሽን አውቃለሁ ፍቅርሽን አክባሪ።
ቀን እረፍት ሳያምረኝ፤ ወይ ሌሊት ምኝታ፤
እርም ብዬ ትቸ ከሰው ጋር ጨዋታ፤
ስፀልይ፤ ስማለል፤ ከጥዋት እስከ ማታ፤
ያሳየኛል ብዬ ዓይንሽን ለአንድ አፍታ።
መከራ ጠግቤ፤ ደስታ እንድራብበት፤ ሌሎት የበሉትን፤ ዕዳ እንድከፍልበት።
መከራ ጠግቤ፤ ደስታ እንድራብበት፤ ሌሎት የበሉትን፤ ዕዳ እንድከፍልበት።
አንጀቴን የበላው፤ አሁን ያሳዘነኝ፤ ታምሜ እማልድነው በሽታ የሆነኝ፤
ሀይለኛው ፍቅርሽ ነው፤ አልረሳም ያለኝ።
እንግዲህ እንተወው ይክተተው ዝምታ፤
ብቻ እንዳትረሽ የፍቅሬን ትዝታ፤ቀን ስትቀመጭ፤ ስትተኝ ማታ።
እንግዲህ ደህና ሁኝ፤ ሁልጊዜ አይለይሽ የእግዚአብሔር ዕርዳታ፤
መከፋት አይንካሽ፤ የልብ ቅሬታ፤ ከለሽበት ሰው ጋር፤ ባለሽበት ቦታ።
እኔ ግን ከእንግዲህ፤ ካንች ከተለየሁ፤ በደስታ እንድትኖሪ እመኝልሻለሁ፤
እኔ ግን ከእንግዲህ፤ ካንች ከተለየሁ፤ በደስታ እንድትኖሪ እመኝልሻለሁ፤
እስኪጠራኝ ድረስ፤ በህይወት እስካለሁ።
October 27, 2009
♦ሰው ለሰው♦
==ሰው ለሰው==
ሆድ ሆድን ሲብሰው፤ ሆድ በሆድ ሲከፋ፤ ቀኑ ዘንበል ሲል፤ ዘንበል ሲል ደፋ፤ የሰው ልጅ ለሰው ልጅ፤ ነው አለንኝታ ተስፋ። ጠጋኝ ድጋፍ ሰጪ፤ ወገን አጋር ሲሻ፤ ቅስሙ ስብር ሲል፤ አለሁ ባይ ወጌሻ። ከሕይወት ውዝግብ፤ ከውጣ ውረዱ፤ ከማጣት ከማግኘት፤ ከመጥላት መውደዱ። ከትርምስ ኑሮው፤ ንፋስ ከሚንጠው፤ በማዕበል እንግልት፤ ከሚብጠለጠለው። ጥግ ከለልላ ሆኖ፤ ትንፋሽ የሚያስጥለው፤ ማረፊያ ወደቡ ለሰው ልጅ፤ ያው ሰው ነው።አቋራጭ ሲፈትሽ፤ ኑሮን ለማሸነፍ፤ ጠጠር ቋጥኝ ሆኖ፤ ከእግሩ ሥር ሲወተፍ።ማፍቀር መውደድ ሲሻ፤ ተፈቅሮ ተወዶ፤ ከአፍቃሪ ከወዳጅ፤ ሲደርስ የጥል መርዶ።ቀኑ ጭልም ሲል፤ ፀሐይ በጧት ወጥታ፤ሊስም የቀረበ፤ በጥፊ ሲመታ። ልብን ሲቃ ይዟት፤ ዓይን እንባ ሲያዘራ፤ ከሰው ወዲያ ለሰው፤ ማን አለ እሚራራ?ማን አለው ለሰው ልጅ፤ ከሰው ወዲያ ለሰው፤በአዘን በደስታ፤ በሁሉ ሚደርሰው፤ ሲስቅ አብሮት ስቆ፤ አንባ አባሹ ለሰው። ነው ውሉ ሰው ለሰው፤ ሰው ከሰው፤ ሰው በሰው፤ አቻ አጋርም የለው፤ ከሰው ወዲያ ለሰው። ሰው ለሰው ነው ጌጡ፤ ሰው ለሰው ነው ክብሩ፤ ሰው ለሰው ነው ተስፋው፤ ሰው ለሰው ነው ፍቅሩ፤የኑሮው ዋስትና፤ ዋልታና ማገሩ።
----------------------------
ትዕግስት ህሩይ፤ መስከረም 05/1991
June 28, 2009
April 23, 2009
April 13, 2009
ዴዚዴራታ፡ Deziderata
አንተ ልዩና ድንቅ ፍጡር በመሆንህ በራስህ ልትደሰት፤ ተገቢውን ክብርና ዋጋም ልትሰጥ ይገባሃል። ማፍቀርም ሆነ መፈቀር የምትችለው ለራስህ ተገቢ የሆነ ፍቅር ሲኖርህ ብቻ ስለሆነ ራስህን ከነድክመትህም ቢሆን ተቀበለው። ፍቅር ለጨለማ መንገድ ብርሀን፤ ለነፍስህም ምግብ ነው። ኑሮህ የሰመረ ይሆን ዘንድ ከሰዎች ሁሉ ጋር ያለህ ግንኙነት ጥንቃቄ አይለየው፤ ለጥፋትህም ሆነ ለልማትህ ሰዎች እጅግ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉና በግንኙነትህ ሁሉ ብልህ ሁን።
ይቀጥላል.........
=============================================================
--------አማኑኤል አለማየሁ---------
-----------------------------------
ዴዚዴራታ ማለት መሰረታዊ የኑሮ መመሪያ ሳይኮሎጅ ማለት ነው።
March 2, 2009
Subscribe to:
Posts (Atom)

