May 28, 2016

በራስ መተማመን


ተደጋጋሚ ውድቀት ቢደርስብዎትም፤ ከግብዎ ለመድረስ አያመንቱ።
ምንጊዜም በጐ ተምኔትን ስንቅዎ መማድረግ ወደፊት ይጓዙ። 
በምድር ላይ ውጥንዎን ስኬታማ ከማድረግ የሚገታዎ አንዳችም ኃይል እንደሌለ ይገንዘቡ።
ታዲያ ዓላማዎ ሃቀኛ ተልዕኮን መንተራስ እንዳለበት አይዘንጉ።
 የማያወላውል አቋምን /ፅናት/ የትግል መሣሪያዎ ይሁን።

ከሁሉም በላይ በራስዎ ይተማመኑ።
 ሊደናቀፉ ይችሉ የሆናል። 
ቢወድቁም እንኳ እዚያው እንደማያሸልቡ በቆራጥኝነት ለራስዎ ያረጋግጡ።
 በማያሰልስ ጥረትዎ መከራና ችግርን ከተጋፈጡ፤ በመጨረሻ ግብዎን መምታትዎ አይቀሬ ነው።
የተፈጥሮ ህግም እንደዚህ ያለውን ብርታት መጠየቁ አያስወቅሰውም። 

እናም እልህ አስጨራሽ ትግል ቢያጋጥምዎም እንኳ፤ 
ከዓላማዎ ፈቀቅ አይበሉ።
 ወደ ግብዎ መቃረብዎን ባያረጋግጡም እንኳ፤ 
አንዲት እርምጃ ወደኋላ አይጓዙ። 
ምሁራኑ "የዕድገት ምስጢር በውድቀት ውስጥ ይገኛል" ይላሉ።
 ድልና ውድቀት፤ ደስታና ሃዘን፤ መዓልትና ሌሊት... 
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። 
ስለዚህ አንዱን ከሌላው ነጥሎ ማንገብ አይቻልም።
አንዱ ባለበት ሥፍራ ሌላውም በግልባጩ ይገኛል።
 ይህ የተፈጥሮ ህግ ነው። 
የተፈጥሮን ህግ መጣስ ባለመቻላችን ልናዝንና ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም።
 በራሳችን ከተማመንን፤ ትግላችን መራራ ቢሆንም እንኳ፤ ግባችን ሩቅ አይሆንም። 

No comments: