April 29, 2016

ናፍቆት

==ናፍቆት==

በእኔና አንቺ መሀል፤ ወንዝ አለ መራራ፣
አላገናኝ አለኝ፣ ሆኖኝ ባላንጋራ።
ያዘኝ ድህነቴ፤ ድልድይ እንዳልሠራ፣
ዋኝቼ እንዳልመጣ ውሀ ልቤ ፈራ፡፡
አንቺ ወዲያ ማዶ፣ እኔ ወዲህ ማዶ፤
ልባችን በስሜት ርቀቱን ጥሶ፣ ገደሉንም ንዶ።
ልዩነት-ጅረትም ፈ'ሶ፤ ወርዶ፤ ወርዶ፤
ቀን ሳይሞላ አይቀርም ለ'ኛ ተዋኅዶ፡፡
እስቲመቸኝ ድረስ፣ እስቲመችሽ ድረስ፤ እስከዚያ ልጨነቅ፤
እስቲመጣ ጊዜ፤ ያንን ወንዝ የሚያደርቅ።
የስሜቴን ምሥጢር እስተዚያ ልደብቅ፣
ያንን ፈገግታሽን፤ እነዚያ ዓይኖችሽን፤ በናፍቆት ልጠብቅ፡፡

እንጉርጉሮ፤ በመስፍን ወ/ማርያም።

No comments: