ምንጭ አልባ አንደበቶች
-የሰውን ማንነት ለማወቅ ከፈለክ፤ መጀመሪያ ስለራስህ ማንነት ማወቅ አለብህ።
-ጭንቀትህን በሥራ ተካውና ተዓምር ሲፈጠር ተመልከት።
-ፍቅር በጥናት እንጂ በቅናት አትቃናም።
-ሰምተህ ሳይሆን አይተህ እርግጠኛ ሁን።
-ጀምበር በማጣትህ ካለቀስክ ከዋክብቶች ይሰወሩብሃል።
-መልካም መስተንግዶ የልባዊ ፍቅር ነፀብራቅ ነው።
-በቀላሉ የምንከዳው በሚያፈቅሩን ጓደኞቻችን ነው።
-ቅን አመለካከት ይኑርዎት፤ ሰዎች እንዲያከብርዎት አስቀድመው ያክብሯቸው።
-የሰው ልጅ ከራስ ወዳድነት፤ ከሱሰኝነትና ከምቀኝነት ከራቀ ሰላምና ፍቅር አግኝቶ ያለፀፀት በነፃነት ሊኖር ይችላል።
-አለመማር አለመኖር ነው።
No comments:
Post a Comment