January 14, 2011

ከጥቅሶች አምባ


* በመጀመሪያ ራስህን እወቅ ጠንካራ ጐንህም ይበልጥ አጠንክር፤ በደካማም ጐኖችህ ላይ ፈጥነህ ዝመት።
* ሰዎችን ከስህተት መልስ እንጅ ወደ ስህተት መንገድ አትምራቸው።
* የሚሠራ ሰው ይሳሳታል የሚያውቅም ያጠፋል፤ አንተ ግን በቅን መንፈስ አስተምረው።
* እውነተኛ ፍቅር ከገንዘብና ከማንኛውም ዓይነት ስልጣን በላይ እጅግ አስደሳች ነው።
* ጥፋትን መናገር ማለት የቤትን ቆሻሻ በመጥረጊያ ሙልጭ አድርጐ ማፅዳት ማለት ነው።
* ፍቅር የአዕምሮ በሽታ ነው፤ ህክምናም አይፈውሰውም መድኃኒቱ እሱ ወይም እሷ ናት።

ምንጭ አልባ አንደበቶች


-የሰውን ማንነት ለማወቅ ከፈለክ፤ መጀመሪያ ስለራስህ ማንነት ማወቅ አለብህ።
-ጭንቀትህን በሥራ ተካውና ተዓምር ሲፈጠር ተመልከት።
-ፍቅር በጥናት እንጂ በቅናት አትቃናም።
-ሰምተህ ሳይሆን አይተህ እርግጠኛ ሁን።
-ጀምበር በማጣትህ ካለቀስክ ከዋክብቶች ይሰወሩብሃል።
-መልካም መስተንግዶ የልባዊ ፍቅር ነፀብራቅ ነው።
-በቀላሉ የምንከዳው በሚያፈቅሩን ጓደኞቻችን ነው።
-ቅን አመለካከት ይኑርዎት፤ ሰዎች እንዲያከብርዎት አስቀድመው ያክብሯቸው።
-የሰው ልጅ ከራስ ወዳድነት፤ ከሱሰኝነትና ከምቀኝነት ከራቀ ሰላምና ፍቅር አግኝቶ ያለፀፀት በነፃነት ሊኖር ይችላል።
-አለመማር አለመኖር ነው።